Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ምርቶች አቅርቦት እጥረት አንዳያጋጥም መንግስት ለህብረት ስራ ማህበራት የ800 ሚሊየን ብር ብድር ማመቻቸቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሚቀጥሉት ጊዜያት የግብርና ምርቶች አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም መንግስት ለተለያዩ ህብረት ስራ ማህበራት የ800 ሚሊየን ብር ብድር አመቻችቶ ወደ ስራ መግባቱ ተገለፀ።

የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ኡስማን ሱሩር፥ ከኮቪድ 19 ስርጭት ከፍ ማለት ጋር ተያይዞ የግብርና ምርቶች አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ዋና ዳይሬክተር ኡስማን ሱሩር፥ በኮቪድ 19 ስርጭት ምክንያት በሚፈለገው ደረጃ አርሶ አደሩ ተንቀሳቅሶ ምርቱን ለሚፈልገው ሸማች ማድረስ በማይችልበት በአሁኑ ወቅት በዘርፉ የሚታዩ የፋይናንስ እጥረትን ለመቅረፍ የተሄደበት ስራ አበረታች መሆኑን ጠቅሰዋል።

ባለፉት አራት ወራትም ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል በላይ የግብርና ምርቶች ተጠቃሚዎች ጋር ማድረስ መቻሉንም ዳይሬክተሩ አንስተዋል።

በቀጣይም የግብርና ምርቶች አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም መንግስት ለተለያዩ ህብረት ስራ ማህበራት የ800 ሚሊየን ብር ብድር ማመቻቸቱን እና እየተሰራበት መሆኑንም አስታውቅዋል።

የአማራ ክልል ህብረት ስራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ የህብረት ስራ ማህበራት የግብይት ዳይሬክተሩ አቶ አለም ዘውድ ስሜነህ በበኩላቸው፥ በቀጣይነት የግብርና ምርት አቅርቦት ችግር እንዳይፈጠር እንዲሁም የዋጋ ንረትን ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

በዚህም የክልሉ መንግስት ባመቻቸው የ170 ሚሊየን ብር ምርቶችን የማቅረብ እና ለቀጣይ ጊዜያትም የመሰብሰብ ስራ ጎን ለጎን እየተሰራበት ነው ብለዋል።

በዚህም በኢኮኖሚ ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች ቀዳሚ ትኩረት የተሰጣቸው መሆኑንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በአፈወርቅ አለሙ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.