የሀገር ውስጥ ዜና

እነ አቶ ጃዋር መሀመድ ዳኛ ይቀየርልን ሲሉ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

By Tibebu Kebede

August 12, 2020

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) እነ አቶ ጃዋር መሀመድ ዳኛ ይቀየርልን ሲሉ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ፡፡

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እነ አቶ ጃዋር ባቀረቡት አቤቱታ ላይ መርምሮ ብይን ሰጥቷል፡፡

በዚህም አቤቱታው በማስረጃ የተደገፈ አይደለም በሚል ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጎታል፡፡

ይህን ተከትሎም ችሎቱ ከዚህ በፊት በነበረው ዳኛ የሚታይ ይሆናል ተብሏል፡፡

በእነ አቶ ጃዋር መዝገብ 14 ሰዎች በዛሬው እለት ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም ዳዊት አብደታ የተባለው ተጠርጣሪ በኮቪድ19 ተጠርጥሮ ችሎት አልቀረበም፡፡

እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ከትናንት በስቲያ ዳኛው ከመዝገባችን ይነሳልን ሲሉ አቤቱታ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

በታሪክ አዱኛ