ስፓርት

በዩሮፓ ሊግ ሲቪያ እና ሻካታር ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል

By Tibebu Kebede

August 12, 2020

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩሮፓ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት ተካሄደዋል፡፡

በጀርመን እየተደረገ ባለው ውድድር የስፔኑ ሲቪያ እና የዩክሬኑ ሻካታር ዶኔስክ ግማሽ ፍጻሜ መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ከእንግሊዙ ወልቨርሃምፕተን ወንደረርስ ጋር የተጫወተው ሲቪያ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

በጨዋታው ወልቭሶች አዳማ ትራኦሬ ተጠልፎ ያገኙትን የፍጹም ቅጣት ራውል ጂሜኔዝ አባክኖታል፡፡

ለሲቪያ ኦካምፖስ በጨዋታው መጠናቀቂያ ላይ የማሸነፊያዋን ጎል አስቆጥሯል፡፡

በሌላ ጨዋታ ሻካታር ዶኔስክ ባዜልን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፎታል፡፡

ለሻካታር ሞራኤስ፣ ታይሰን፣ ሎሬንኮ እና ዶስ ሳንቶስ የድል ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ ወልፍስዊንከል ለባዜል ማስተዛዛኛዋን አስቆጥሯል፡፡

በግማሽ ፍጻሜው ሲቪያ ከማንቼስተር ዩናይትድ እንዲሁም ሻካታር ከኢንተር ሚላን ይገናኛሉ፡፡