የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ በህገ ወጥ የመሬት ወረራና ግንባታ ላይ እርምጃ መውሰድ ተጀመረ

By Tibebu Kebede

August 12, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተስተዋለ ባለው ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ግንባታ ላይ እርምጃ መወሰድ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ አስታወቁ።

በከተማዋ በተለይም በማስፋፊያ ክፍለ ከተምች ላይ እየተዛመተ የመጣውን የመሬት ወረራ ለማስቆም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የተወረሩ መሬቶችን የማስመለስ ስራ ተጀምሯል ብለዋል ምክትል ከንቲባው።