የሀገር ውስጥ ዜና

በ24 ሰዓታት 943 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ23 ሰዎች ሕይወት አልፏል

By Tibebu Kebede

August 12, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 14 ሺህ 540 የላብራቶሪ ምርመራ 943 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ይህን ተከትሎም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 25 ሺህ 118 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባወጡት መረጃ አመላክተዋል።