Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረሰ በአምራች ሃይሉ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ትኩረት ሊደረግ ይገባል- የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮና ቫይረሰ በአምራች ሃይሉ ላይ ከፍ ያለ ጉዳት እንዳያደርስ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች አስታወቁ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች፥ የቫይረሱ ስርጭት ተጽእኖ በምጣኔ ሃብቱ ላይ ከፍ ያለ ጉዳት እንዳያደርስ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አንሰተዋል።

የኢኮኖሚው አንቀሳቃሽ የሆነዉ አምራች ሃይል ራሱን ከቫይረሱ ሊጠብቅና ሃላፊነቱነ መወጣት እንዳለበትም ባለሙያዎቹ ተናግረዋል።

በባሀር ዳር ዮኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክሰ መምህርና ተመራማሪ ዶክተር ዳረጎት በሪሁን፥ ይህ አደገኛ የጤና እክል በግለሰብ ደረጃ የሚያሳደረው ተጽእኖ ከፍ እስካለው ሃገራዊ ኢኮኖሚ ድረስ የተሳሰረ እንደሆነ ያነሳሉ።

ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጡ ምክሮችን ተግባራዊ ማድረግ ሀገርን ከምጣኔ ሃብት ቀውስ መታደግ ነው፤ ይህ አማራጭ የሌለው የቤት ስራ ደግሞ ኢትዮጵያን ለመሰሉ ደሃ ሀገራት ዜጎች የሰርክ ተግባር እንዲሆን ይጠበቃል ብለዋል።

ሌላው ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የምጣኔ ሃብት ባለሙያ አቶ ዋሲሁን በላይ፥ ኢትዮጵያ እያጋጠማት ያለውን የኢኮኖሚ መንገራገጭ ለመጠገን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት አሁን ካለበት ከፍ እንዳይል ትኩረት ልትሰጠው ይገባል ብለዋል።

የማህበራዊ ምጣኔ ሀብት ጉዳዮች ተንታኝ የሆኑት አቶ ዋሲሁን በላይ፥ “በክፍተትነት የሚነሳው መዘናጋት ዋጋ እንዳያስከፍለን መንቃት አለብን” ይላሉ።

የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ፥ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት እና በድህረ ኮሮና ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት የሚያስችሉ ስራዎችን በትክክል ተግበራዊ ማድረግ ተጠባቂ ስራ እንደሆነ ይናገራሉ።

የተዛቡ የገበያ ስርአቶች በመሰል ወቅት በማሀበረሰቡ ላይ የሚያሳድሩት ተጽእኖ ሌላኛዉ የትኩረት ነጥብ ነው።

አለም አቀፍ የምጣኔ ሃብት እና ንግድ ግንኙነቶችን ማሳደግ እንደሚገባም ያነሱት ባለሙያዎቹ፥ የግሉ ዘርፍም ቢሆን አምራች ሀይሉ ራሱን ከቫይረሱ እንዲጠብቅ ለሙያተኛው ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል።

ከፍተኛ የሆነው የህዝብ ቁጥር የሚገኝበት በገጠሩ ክፍል ወረርሽኙ እንዳይስፋፋ አሁንም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተመላክቷል።

በአወል አበራ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.