ኮሮናቫይረስ

በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ብቻ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

By Meseret Demissu

August 13, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 14 ሺህ 688 የላብራቶሪ ምርመራ 1086 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከዚህም ባለፈ የ16 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 479 መድረሱንም አመላክተዋል።