Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በሸገርን ማስዋብ ስራ ላይ ለተሰማሩ አካላት ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሸገርን ማስዋብ ስራ ላይ ለተሰማሩ አካላት ምስጋና አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ የከተማችን ገፅታ የላቀ ለውጥ እንዲያሳይ ላደረጉ እና ገንዘባቸውን፣ ጊዜያቸውን እና ጉልበታቸውን ሳይቆጥቡ ያፈሰሱትን ጥቂት ደፋር ሰዎች አለማመስገን አይቻልም ብለዋል፡፡

አዎንታዊ ውጤት ከፍጻሜ ይደርስ ዘንድ፣ ጥቂት ቆራጦችን ይጠይቃል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፈለጉት ውጤት እንደሚገኝ ማስተማመኛ ሳይኖራቸው በእምነት የሚራመዱ ጥቂት ደፋሮች እንደሚያስፈልጉም አንስተዋል።

መሰል ሥራዎች በክልሎችም እንደሚቀጥል ጠቅሰው፤ ሌሎችም ይህንን የ’ጥቂት ደፋሮች’ ቡድን እንዲቀላቀሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.