Fana: At a Speed of Life!

የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ከ16 አመት በኋላ ተሰበረ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ትናንት ማታ በዑጋንዳዊው አትሌት ቼፕቴጌ ተሻሽሏል፡፡

ጆሹዋ ቼፕቴጌ ትናንት ምሽት በሞናኮ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር የ5 ሺህ ሜትሩን ክብረ ወሰን በሁለት ሰከንዶች አሻሽሎታል፡፡

አትሌቱ ርቀቱን 12 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ ከ36 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ ነው ክብረ ወሰኑን ማሻሻል የቻለው፡፡

የወንዶች 5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን በኢትዮጵያዊው ቀነኒሳ በቀለ ላለፉት 16 አመታት ተይዞ የቆየ ነበር፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.