የሀገር ውስጥ ዜና

23 ሺህ ግራም ወርቅ በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ ሲል ተያዘ

By Tibebu Kebede

August 15, 2020

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በትናትናው ዕለት 46 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያለው 23 ሺህ ግራም ወርቅ ከሀገር ሊወጣ ሲል መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

23 ሺህ ግራም ወርቁ ናይጄሪያ ዜግነት ባለው ግለሰብ ከሀገር ሊወጣ ሲል በቦሌ አየር መንገድ መያዙን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።