የሀገር ውስጥ ዜና

በአንድ ቀን ብቻ በኢትዮጵያ 1 ሺህ 652 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል

By Tibebu Kebede

August 15, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 22 ሺህ 252 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 652 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የዛሬው ውጤት በሀገሪቱ በአንድ ቀን ብቻ የተመዘገበ ከፍተኛ ቁጥር ሆኗል። ይህንን ተከትሎም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 28 ሺህ 894 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባወጡት መረጃ አመልክተዋል።