Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ አፍሪካ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የጣለቻቸውን ገደቦች ልታላላ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 10፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት የኮሮና ቫይረስ በአገሪቱ እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ የወጡትን ገደቦች ከሰኞ ጀምሮ ቀለል እንደሚሉ ገለፁ፡፡

ፕሬዝዳንት ሴሪል ራማፎሳ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያሉ ሁሉም ገደቦች እንደሚላሉ ተናግረዋል ፡፡

የሃገር ውስጥ ጉዞ ፣ አነስተኛ የቤተሰብ ስብሰባዎች እና ንግዶች ክፍት እንደሚሆኑም ተነግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ እንደተናገሩት የእገዳው መላላት አገሪቱ ከደረሰባት ችግር በኋላ ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት የሚረዳ ነው ፡፡

ሆኖም ደቡብ አፍሪካውያን አሁን የሚታዩ “የተስፋ ምልክቶች” ቢኖሩም ወደፊት የሚመጣውን አስቸጋሪ ጊዜ በመጠንቀቅ ለቫይረሱ ላለመጋለጥ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አገሪቱ እስካሁን ከ570 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ሲያዙ ከ11 ሺህ 500 የሚልቁ ሰዎች ሞተዋል፡፡

ደቡብ አፍሪካ በአለም አቀፍ ደረጃ ከአሜሪካ፣ ብራዚል፣ ሩሲያ እና ህንድ ቀጥሎ ቫይረሱ የጸናባት ሃገር በመሆን አምስተኛ ደረጃን ከያዘች ሰንበትበት ብላለች፡፡

ሆኖም በአሁኑ ወቅት በቀን ከሚያዙት 12 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ 5 ሺህ ዝቅ ማለቱን ተከትሎ እገዳዎችን ቀለል ማድረግ እንደተቻለ ነው ፕሬዚዳንቱ የጠቆሙት፡፡

በተጨማሪም ከቫይረሱ የሚያገገሙ ሰዎች ቁጥር ወደ 80 በመቶ ከፍ ማለቱንም ተናግረዋል ፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.