Fana: At a Speed of Life!

‘’ገበታ ለሃገር’’ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 10፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የገበታ ለሃገር መርሃ ግብር ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለኢትዮጵያ ብልጽግና አሻራቸውን የሚያኖሩበት ነው ተብሏል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገበታ ለሃገር ይፋ በተደረገበት ወቅት ገንዘብ፣ እውቀት እና ጉልበት በማሰባሰብ ተፈጥሮን ሳናውክ ለዜጎችም ለውጭ ቱሪስቶችም የምትመች ኢትዮጵያን እንፈጥራለን ብለዋል፡፡

በገበታ ለሃገር መርሃ ግብር በጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንታት የVVIP እና VIP የተከፈለበት የእራት ግብዣ ይኖራል፡፡

VVIP 10 ሚሊዮን ብር ሲሆን VIP 5 ሚሊዮን ብር ይከፈልበታል ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ብልጽግና ውስጥ ሁሉም ዜጋ አሻራውን እንዲያኖርም በኢትዮ-ቴሌኮም አማካኝነት የአጭር የጽሁፍ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያ ይዘጋጃል፡፡

ዲያስፖራውም ድጋፍ እንዲያደርግ ገንዘብ የሚሰበሰብበት አካውንት ይከፈታል ተብሏል፡፡

በጥቅሉ ከገበታ ለሃገር ቢያንስ 3 ቢሊየን ብር ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሚገኘው ሃብትም ጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻ በሚቀጥለው ዓመት ይለማሉ ተብሏል፡፡

“ገበታ ለሃገር” እና “ገበታ ለሸገር” ከአዲስ አበባ ተሻግሮ በመላው ኢትዮጵያ የሚሰፋበት ነው፡፡

በአልአዛር ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.