Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ለእስራኤልና ለተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለእስራኤልና ለተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

እስራኤልና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ባሳለፍነው ሀሙስ መደበኛ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለመመስረት ከስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድም ይህንን ተከትሎ ነው በዛሬው እለት በኢፌዴሪ መንግስት እና በራሳቸው ስም ለሁለቱም ሀገራት የደስታ መግለጫ መልእክት ያስተላለፉት።

በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክታቸውም ሀገራቱ ሰላማዊ ግንኙነትን በድጋሚ ለማስጀመር የወሰዱት እርምጃ በዓለም ዙሪያ ሰላምና መረጋጋትን ለማስጠበቅ ለሚደረጉ ጥረቶች ወሳኝ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በመልእክታቸው አክለውም፤ “ወንድሜ ልዑል መሀመድ ቢን ዘይድ አል-ናህያን ለሚሰጡት አመራር አመሰግናቸዋለሁ፤ በመካከለኛው ምስራቅ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የተጀመረው ጉዞ እንደሚሳካ እምነታቸው መሆኑንም ጠቅሰዋል።

እስራኤልና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መደበኛ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለመመስረት ባሳለፍነው ሀሙስ ነበር ከስምምነት የደረሱት።

እስራኤል እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የደረሱት ስምምነት እስራኤል ነፃነቷን በ1948 ካወጀች በኋላ 3ኛው የእስራኤል አረብ የሰላም ስምምነት መሆኑ ታውቋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.