Fana: At a Speed of Life!

በሶማሊያ በተፈጸመ ጥቃት 17 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 11፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በተፈጸመ ጥቃት 17 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ፡፡

በመዲናዋ የባህር ዳርቻ አካባቢ በሚገኝ ሆቴል ላይ በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ ቦምብ በተጀመረው ጥቃት በርካቶች መቁሰላቸውም ነው የተነገረው፡፡

ጥቃቱ በአልሸባብ የተፈጸመ መሆኑን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

የቡድኑ ታጣቂዎችም ወደ ሆቴሉ በመግባትና ተጠቃሚዎችን በማገት ከመንግስት የፀጥታ አካላት ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርገዋል ነው የተባለው፡፡

በተኩስ ልውውጡም የፀጥታ አካላት፣ የሆቴሉ አስተናጋጆች እና ተጠቃሚዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ታውቋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የቡድኑ አራት ተጣቂዎችም በፀጥታ አካላት ተገድለዋል፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.