ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስዊዘርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከስዊዘርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢግናዚኦ ካሲስ ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸው በሃገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ትኩረት አድርገው መክረዋል።
በቀጣይም ሃገራቱ በተለያዩ ዘርፎች በሚኖራቸው የትብብርና የግንኙነት ማዕቀፍ ዙሪያ በትኩረት ለመስራት መስማማታቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ውይይቱ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ እየተካሄደ ካለው ዓለም አቀፉ የስደተኞች ፎረም ጎን ለጎን የተደረገ ነው።
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ በዓለም አቀፉ የስደተኞች ፎረም ላይ ለመሳተፍ ከትናንት በስቲያ ወደ ስዊዘርላንድ ማቅናቱ ይታወሳል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንም ከፎረሙ ጎን ለጎን ከዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።