Fana: At a Speed of Life!

የግሉ ዘርፍ ፈጠራ በታከለበት መንገድ ምርቶችን በማዳበር በቡና ኢንዱስትሪው ቢሰማራ የላቀ ውጤት ያስገኛል- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 12 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የግሉ ዘርፍ ፈጠራ በታከለበት መንገድ ምርቶችን በማዳበር በቡና ኢንዱስትሪው ቢሰማራ የላቀ ውጤት እንደሚስገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያን ቡና እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ የሚቀርብ ድርጅት ጎብኝተዋል።

ቡና የኢትዮጵያ ወርቅ እና የባሕላዊ ትሥሥር ምንጭ መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለውጭ ገበያ ከምናቀርባቸው ዋነኛ ምርቶች መካከል አንዱም ነው ብለዋል።

የግሉ ዘርፍ በቴክኖሎጂ በመታገዝ፣ ዕውቀትን በመቅሰም፣ ፈጠራ በታከለበት መንገድ ምርቶችን በማዳበር ዕሴቶችን በመጨመር በቡና ኢንዱስትሪው ቢሰማራና ሙዓለ ንዋይ ቢያፈስስ የላቀ ውጤት ያስገኛል ሲሉ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.