የሀገር ውስጥ ዜና

የግሉ ዘርፍ ፈጠራ በታከለበት መንገድ ምርቶችን በማዳበር በቡና ኢንዱስትሪው ቢሰማራ የላቀ ውጤት ያስገኛል- ጠ/ሚ ዐቢይ

By Tibebu Kebede

August 18, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 12 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የግሉ ዘርፍ ፈጠራ በታከለበት መንገድ ምርቶችን በማዳበር በቡና ኢንዱስትሪው ቢሰማራ የላቀ ውጤት እንደሚስገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያን ቡና እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ የሚቀርብ ድርጅት ጎብኝተዋል።