የሀገር ውስጥ ዜና

የብልጽግና ፓርቲ ያለፉ መልካም ተሞክሮዎችን በማጠናከር ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግና አሳታፊ ዴሞክራሲ እንደሚገነባ ተገለፀ

By Tibebu Kebede

December 18, 2019

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ዝቅተኛ አመራሮች በብልጽግና ፓርቲ ዙሪያ ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡

በዚህ ወቅት የብልፅግና ፓርቲ ያለፉ መልካም ተሞክሮዎችን በማጠናከር ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ እና አሳታፊ ዴሞክራሲ መገንባት የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።