Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የዕርቀ ሰላም ኮሚሽን በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱ በአቅም ግንባታ፣ በሀብት አጠቃቀም፣ በመረጃ ልውውጥ፣ በልምድ ልውውጥ እና ተዛማጅነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የግጭት መንስዔዎችን ማጥናት፣ ግጭቶች የሚፈቱበትን ሀሳብ ማቅረብ፣ ብሔራዊ መግባባት እና የመሳሰሉት ኃላፊነቶች ሁለቱን ተቋማት የሚያስተባብሯቸው የጋራ ጉዳዮች ናቸው ተብሏል።

የስምምነቱ ዋና ዓላማ ሁለቱ ወገኖች በሚጋሯቸው ራዕዮች እና ግቦች ዙሪያ በታቀደ እና በተቀናጀ ሁኔታ ተባብረው ጊዜ፣ ገንዘብ እና ጉልበትን በቆጠበ መልኩ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን መሆኑም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.