ስፓርት

ሮናልድ ኪዩመን ባርሴሎናን በአሰልጣኝነት ተረከበ

By Tibebu Kebede

August 19, 2020

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የስፔኑ ባርሴሎና ሮናልድ ኪዩመንን አሰልጣኙ አድርጎ ሾሟል፡፡

የካታላኑ ክለብ የቀድሞ አሰልጣኙ ኪኬ ሴቲዬንን ከቻምፒየንስ ሊጉ ሽንፈት በኋላ አሰናበቷል፡፡

ይህን ተከትሎም የቀድሞው የክለቡን ተጫዋች ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል፡፡

ኪዩመን የኔዘርላንድስ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ እንደነበር አይዘነጋም፡፡