Fana: At a Speed of Life!

በሻሸመኔ ዛሬ ጠዋት በጸጥታ አስከባሪዎች ላይ ቦምብ በወረወረ የኦነግ ሸኔ አባል ላይ እርምጃ መወሰዱን ፖሊስ ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በሻሸመኔ ከተማ የውስጥ ለውስጥ የጸጥታ ስራን በማከወን ላይ በነበሩ ጸጥታ አስከባሪዎች ላይ ቦምብ በወረወረ የኦነግ ሸኔ አባል ላይ እርምጃ መወሰዱን ፖሊስ ገለፀ።

ዛሬ ከጠዋቱ አንድ ሰአት ተኩል አከባቢ በሻሸመኔ ከተማ 01 ወይም አዋሾ ቀበሌ አካባቢ የጸጥታ ሀይሎች አካባቢያዊ ዳሳሳ ቅኝት ሲያደርጉ ነው ከድር ቱሌ የተባለ ግለሰብ የእጅ ቦምብ ወርውሮ ሊያመልጥ ሲል እርምጃ የተወሰደበት።

በዚህም የተጠርጣሪው ህይወት ሲያልፍ ቦምብ ከተወረወረባቸው የጸጥታ ሀይሎች መካከል በአንዱ ላይ ጉዳት ደርሶ በመልክ ኦዳ ሆስፒፕታል ክትትል እየተደረገለት መሆኑ ተገልጿል።

የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፀው፥ ከተጠርጣሪው እጅ ተጨማሪ የጦር መሳሪያ ተገኝቷል።

ከድር ቱሌ የተባለው ይህ ተጠርጣሪ መታወቂያው የአርሲ ዞን ሸርካ ወረዳ ነዋሪ እንደሆነ የሚያሳይ ሲሆን፥ ሁለት ሞባይል፣ ገንዘብ እና ትጥቅ መያዣ ቀበቶ ይዞ ነበር።

የከተማው ፖሊስ መምሪያ ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይል እንዲሁም ከፌደራል ፖሊስና ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በጥምረት እየሰራ መሆኑንም ነው ያስታወቀው።

የሻሸመኔ ከተማ አሁን ላይ ወደ ቀድሞ ሰላማዊ እንቅስቃሴዋ እየተመለሰች ሲሆን፥ ከዚህቀደም ለወደሙና ጉዳት ለደረሰባቸው ድጋፍ የማድረጉ ተግባርም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የከተማዋ ነዋሪ ከጸጥታ አካሉ ጋር ተናቦ እየሰራ ባለው ስራ በርካታ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ያለው ፖሊስ የተዘረፉ ንብረቶችም እየተመለሱ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

በሃይለየለሱስ ስዩም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.