Fana: At a Speed of Life!

አዋሽ ባንክ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የ25 ሚሊየን ብር ቦንድ ገዛ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አዋሽ ባንክ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የ25 ሚሊየን ብር የቦንድ ግዢ አከናወነ።

ባንኩ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ቦንድ በመግዛትና ገንዘብ በመለገስ አስፈላጊውን የፋይናንስ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቆ፤ “ፕሮጀክቱ ላይም የራሱን አሻራ እያኖረ መበሆኑ እንደሚያስደስተው ገልጿል።

ስለሆነም ልክ እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ ግድቡ ተጠናቆ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የድርሻውን እንዲያበረክት በባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድና የስራ አመራር ውሳኔ መሰረት የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ 25 ሚሊየን የቦንድ ግዢ ማከናወኑን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.