የአውስትራሊያ አየር መንገድ 2 ቢሊየን ዶላር ዓመታዊ ኪሳራ እንዳጋጠመው ገለጸ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 14 ፣ 2012 (ኤፍ. ቢ.ሲ)ኳንታስ የተባለው የአውስትራሊያው አየር መንገድ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ 2 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ዓመታዊ ኪሳራ እንዳጋጠመው ገለጸ።
የኳንታስ ግሩፕ ሥራ አስፈፃሚ አላን ጆይሴ ÷ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የጉዞ ገደቦች ስለተጣሉ በሁሉም አየር መንገዶች ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ ከባድ ነው ብለዋል።
በመሆኑም የኳንታስ አየር መንገድ አሁን ያጋጠመው የንግድ ሁኔታ በ100 ዓመት የአየር መንገዱ ታሪክ አስከፊው ነው ብለዋል።
በዚህም ምክንያት አየር መንገዱ ሰኔ ወር ላይ ከሥራ ሊቀንሳቸው አቅዶት ከነበረው 6 ሺህ ሰራተኞቹ 4 ሺህ ገደማ የሚሆኑት የሥራ ቆይታቸው በሚቀጥለው ወር መጨረሻ ላይ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
ሥራ አስፈፃሚው አያይዘውም በሚቀጥለው በጀት ዓመትም ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
ምንጭ፡-ቢቢሲ
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።