ስፓርት

አቶ ኢሳያስ ጅራ የሴካፋ ምክትል ፕሬዚዳንትነት ሆነው ተመረጡ

By Tibebu Kebede

December 18, 2019

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የሴካፋ ምክትል ፕሬዚዳንትነት ሆነው መመረጣቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

የመካከለኛውና ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የእግር ኳስ ማህበር/ሴካፋ/ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የአባል ሀገራቱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንቶች በተገኙበት በኡጋንዳ ካምፓላ በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡