Fana: At a Speed of Life!

በካሊፎርኒያ ሰደድ እሳት ዳግም ተቀስቅሶ ጉዳት እያደረሰ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ሰደድ እሳት ዳግም ተቀስቅሶ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡

በግዛቲቱ በተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት ስካሁን ስድስት ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውም ነው የተነገረው፡፡

በግዛቲቱ አንዳንድ አካባቢዎች የታየው ሰደድ እሳት እስካሁን ከታዩት ከባድ እና በመጠኑም ሰፊ መሆኑን የግዛቲቱ አስተዳዳሪ ጋቪን ኒውሰም ተናግረዋል፡፡

ሰደድ እሳቱን ተከትሎም ግዛቲቱ ከአውስትራሊያ ድጋፍ የጠየቀች ሲሆን አሁን ላይ ከ12 ሺህ በላይ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ተሰማርተው እሳቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እያደረጉ ነው ተብሏል፡፡

በግዛቲቱ በተለይም በዴዝ ቫሊ ፓርክ በሳምንቱ መጀመሪያ የተመዘገበው የሙቀት መጠንና አሁን ላይ ያለው ደረቅ እና ነፋሻማ አየር ለሰደድ እሳቱ መባባስ ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረም ተነግሯል፡፡

ሌሊቱን በአንዳንድ አካባቢዎች የእሳቱ መጠን በእጥፍ መጨመሩን ተከትሎም እስካሁን 175 ሺህ ሰዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል፡፡

ይሁን እንጅ በግዛቲቱ ካለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ በርካቶች ወደ መጠለያ ጣቢያ የመግባት ፍላጎት እያሳዩ አይደለም ነው የተባለው፡፡

በሰደድ እሳቱ ሳቢያ በርካታ መኖሪያ ቤቶችና ህንጻዎች የወደሙ ሲሆን ረጃጅም የካሊፎርኒያ እድሜ ጠገብ ዛፎችና የወይን እርሻዎችም የእሳቱ ሰለባ እየሆኑ ነው ተብሏል፡፡

አስተዳዳሪው ጋቪን ኒውሰም ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአደጋ ጊዜ አዋጅ እንዲያውጁ እየጠየቁ ነው፡፡

በሰደድ እሳቱ ሳቢያ እስካሁን 1 ሺህ 950 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የግዛቲቱ አካል በእሳት መውደሙን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ምንጭ፤ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.