Fana: At a Speed of Life!

የኮሮናቫይረስ የኢኮኖሚ ተፅእኖን ለመቀነስ መንግስት  የወሰነው የዕዳ ምህረት ተግባራዊ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስትሩ ገለፁ 

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮናቫይረስ የኢኮኖሚ ተፅእኖን ለመቀነስ መንግስት  የወሰነው የዕዳ ምህረት ተግባራዊ መሆኑን የኢፌዴሪ የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ገለፁ።

በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተቀዛቀዘው ኢኮኖሚ እንዲነቃቃ፣ በየድርጅቱ ያሉ ሰራተኞች እንዲቀጥሉ እና ተጨማሪ የስራ ዕድል እንዲፈጠር ለማድረግና ሎሎችንም ምክንያቶች ታሳቢ በማድረግ መንግስት በወሰነው መሰረት የእዳ ምህረቱ ተግባራዊ መደረጉን አመልክተዋል።

ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያወጡት መግለጫ  በእዳ ምህረት መመሪያው መሰረት እስከ 2007 የበጀት አመት የግብር ዕዳ ያለባቸው የፊደራል ግብር ከፋዮች ብር 34 ነጥብ 08 ቢሊየን ብር ግብር ለ2 ሺህ 411 ድርጅቶች ዕዳው እንዲሰረዝ ተደርጓል።

ከ2008 እስከ 2011 የበጀት አመት የግብር ዕዳ ያለባቸው  100 በመቶ በአንድ ጊዜ ፍሬ ግብር ለከፈሉ 1 ሺህ 627 ድርጅቶች ከፍሬ ግብሩ  208 ሚሊየን 676 ሺህ ብር፣ ወለድ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ፣ ቅጣት ከ3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ በድምሩ 5 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ምህረት እንደተደረገላቸው ነው ያስታወቁት።

እነዚህ ድርጅቶች 90 በመቶዎቹ  ለመንግስት 1 ቢሊየን 943 ሚሊየን ብር መክፈላቸውን ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ አቶ ላቀ በሌላም በኩል 794 ድርጅቶች 25 በመቶዎቹ  ቅድሚያ 2 ቢሊየን 240 ሚሊየን ብር መክፈላቸውንና  እነዚህ ድርጅቶች በውላቸው መሰረት ከቀጠሉ ቅጣትና ወለድ የሚነሳላቸው መሆኑን አስረድተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.