Fana: At a Speed of Life!

የትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ ኬሊያን ኮንዌይ ስልጣን ሊለቁ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ኬሊያን ኮንዌይ ስራቸውን እንደሚለቁ አስታወቁ፡፡

የፕሬዚዳንቱ ቀኝ እጅ ናቸው የሚባሉት ኮንዌይ በፈረንጆቹ ነሃሴ ወር መጨረሻ ላይ ከነጩ ቤተ መንግስት እለቃለሁ ብለዋል፡፡

የእርሳቸው ከስልጣን መልቀቅ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቀጣዩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዳግም ለመመረጥ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ ያለ ሁነኛ አማካሪና ቃል አቀባይ ያስቀራቸዋልም ነው የተባለው፡፡
አማካሪዋ ለልጆቻቸው ጊዜ መስጠትን እና ትክክለኛ እናት መሆንን ደግሞ ለመልቀቃቸው ምክንያት አድርገዋል፡፡

በ2016ቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ የተሳካ እንዲሆን ጉልህ ሚና መጫወታቸው ይነገርላቸዋል፡፡

ኬሊያን በትራምፕ አስተዳደር ስር ረጅም ጊዜ በስልጣን የቆዩ የመጀመሪያዋ ሴት ከፍተኛ ባለስልጣን እና በትራምፕ ከስልጣን ሳይባረሩ የቆዩ የፕሬዚዳንቱ ሁነኛ አጋር እንደነበሩ ይነገራል፡፡

ምንጭ፣ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.