የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችን የተሻለ ተጠቃሚየሚያደርግ ”ዩዝ ኮኔክት ኢትዮጵያ” የተሰኘ ሀገራዊ ፕሮግራም ሊጀመር ነው

By Tibebu Kebede

December 19, 2019

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችን የተሻለ ተጠቃሚ የሚያደርግ ”ዩዝ ኮኔክት ኢትዮጵያ” የተሰኘ ሀገራዊ ፕሮግራም በይፋ ሊጀመር ነው፡፡ ሀገራዊ ፕሮግራሙን በይፋ ለማስጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡