በአፋርና ሶማሌ ክልሎች የኤሌክትሪክ ሀይል ለማመንጨት የሚያስችል ስምምነት ከሳዑዲው አክዋ ፓወር ጋር ተፈረመ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፋርና ሶማሌ ክልሎች የኤሌክትሪክ ሀይል ለማመንጨት የሚያስችል ስምምነት በኢትዮጵያ እና በሳዑዲው ዓረቢያው አክዋ ፓወር መካከል ተፈረመ።
ስምምነቱ በመንግስትና በግል አጋርነት በሁለቱ ክልሎች ጋድ እና ዲቼቶ አካባቢዎች ከታዳሽ ሀይል ኤሌክትሪክ ለማመንጨት የሚያስችል ነው ተብሏል።
በ300 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚከናወነው ፕሮጀክት፥ 250 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል ያመነጫል ነው የተባለው።
ከሳዑዲው ዓረቢያው አክዋ ፓወር ጋር የተደረሰው ስምምነት በመንግስት እና በግል አጋርነት በሃይል ዘርፍ ኢትዮጵያ የተፈራረመችው የመጀመሪያው ስምምነት ነው።
በአላዛር ታደለ