ቢዝነስ

ኔዘርላንድስ የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ቀዳሚ መዳረሻ ስትሆን አሜሪካና ሶማሊያ ቀጣዩን ደረጃ ይዛዋል

By Tibebu Kebede

August 25, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኔዘርላንድስ የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ቀዳሚ መዳረሻ ስትሆን አሜሪካ እና ሶማሊያ ቀጣዩን ደረጃ መያዛቸውን የንግድ እና ኢንዱስት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ኔዘርላድስ አበባ ፣ ቡና፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት የኤሌክትሪክ ውጤቶች፣ ጫማ ፣ ቆዳ ማርና ሰም፣ የቅባት እህሎች የአልኮል መጠጦች፣ ጫት፣ ሻይ ብረትና የመሳሰሉትን ከኢትዮጵያ በመቀበል 320 ሺህ 162  የአሜሪካን ዶላር በማስግኘት ቀዳሚ ሀገር ሆናለች ብሏል፡፡