Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ከሳዑዲ የልማት ፈንድ ልዑካን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከሳዑዲ የልማት ፈንድ ተቋም ልዑካን ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዶክተር ካሊድ ኤስ. አልኩዴሪ የተመራውን ልዑክ በዛሬው እለት በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

በዚህ ወቅትም በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ላሉ በርካታ ሥራዎች በሚደረግ የኢንቨስትመንት እና የልማት ድጋፍ ላይ ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሳዑዲ የልማት ፈንድ ዶክተር ካሊድ ኤስ. አልኩዴሪ እና የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴን፥ ለመንገድ ሥራ፣ ውሀ አቅርቦት እና ሳኒቴሽን ልማት የሚውል የ140 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነቶች አፈራርመዋቸዋል።

በተጨማሪም የአኳ ፓወር ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት ፓዳ ፓድማንተን እና የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር አብርሀም በላይን፥ በአፋር ክልል እና በሶማሌ ክልሎች ከፀሐይ ሀይል ማመንጨት እና የሀይል ግዢ ስምምነትንም አፈራርመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.