Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያዊው ዶክተር ዮሃንስ በ2019 በሳይንሱ ዓለም አስፈላጊ ከተባሉ 10 ሰዎች ውስጥ አንዱ ሆኑ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው የሰው ልጅ አመጣጥና የማህበረሰብ ተመራማሪ ዶክተር ዮሃንስ ሀይለሥላሴ በፈረንጆቹ 2019 በሳይንሱ ዓለም አስፈላጊ ከተባሉ 10 ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ።

ተመራማሪው በታዋቂው ኔቸር ጋዜጣ ሊጠናቀቅ ቀናት በቀሩት የፈረንጆቹ 2019 በሳይንሱ ዓለም ከ10 ተፈላጊ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል።

ዶክተር ዮሃንስ በኢትዮጵያ ከ2 ነጥብ 5 እስከ 5 ነጥብ 8 ሚሊየን እድሜ ያላቸውን ጥንታዊ የሰው ልጅ ቅሪተ አካላት ያገኙ ተመራማሪም ናቸው።

እርሳቸው ያገኟቸው ቅሪተ አካሎች ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ መሆኗን የሚያጠናክሩ ግኝቶች ስለመሆናቸውም ይነገራል።

በእርሳቸውና ባልደረቦቻቸው ከተገኙ ቅሪተ አካሎች መካከል የሉሲ ቅድመ አያት እንደሆነ የሚታመነው ቅሪተ አካል በዋናነት ይጠቀሳል።

ዶክተር ዮሃንስ ሀይለሥላሴ በክሌቭላንድ የሰው ልጅ አመጣጥና የማህበረሰብ ተመራማሪ በመሆን ያገለግላሉ።

በዚህ ዘርፍ ከሰው በተጨማሪ በተለይም በአፋርና አዋሽ አካባቢ ባደረጉት ጥናትና ምርምር ሚሊየን አመታት ያስቆጠሩ የተለያዩ እንስሳት ቅሪተ አካል ማግኘት ችለዋል።

እነዚህና በዘርፉ እያበረከቱት ባለው አስተዋጽኦ ሳቢያም በፈረንጆቹ 2019 በሳይንሱ ዓለም አስፈላጊ ከተባሉ 10 ሰዎች መካከል ተካተዋል።

ከእርሳቸው በተጨማሪ የአየር ንብረት ተሟጋቿ ስዊድናዊቷ የ16 አመት ታዳጊ ግሬታ ተንበርግ እና ብራዚላዊው የፊዚክስ ተመራማሪ ሪካርዶ ጋልቫኦ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል።

ምንጭ፦ www.wksu.org/

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.