Fana: At a Speed of Life!

ታንዛኒያ 15 ፕሬዚዳንታዊ እጩዎችን ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ታንዛኒያ በመጪው ጥቅምት ወር ለምታካሄደው ምርጫ 15 ፕሬዚዳንታዊ እጩዎች መቅረባቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ቦርድ ይፋ አደረገ።

በአውሮፓውያኑ 2015 ሙስናን እወጋለሁ መሰረተ ልማትን አስፋፋለሁ በማለት ወደ ስልጣን የመጡት ጆን ማጉፍሊ ለሁለተኛ ጊዜ አገሪቱን ለመምራት እንደሚወዳደሩ ተገልጻል።

ጥቅምት 18 በሚደረገው ፕሬዚዳንታዊና ፓርላሜንታዊ ምርጫ በቅጽል ስማቸው ቡልዶዘር በመባል የሚጠሩት ጆን ማጉፍሊ በድጋሚ እንደሚያሸንፉ ከወዲሁ ግምት ተሰጥቷቸዋል።

ለዚህም በሀገሪቱ የሚገኙ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ወደ ምርጫ የሚያደርጉት ጉዞ የተናጠል መሆኑ እንደምክንያት ተነስቷል።

እንዲሁም ከአምስት ዓመታት በፊት በተካሄደው ምርጫም የማጉፍሊ ፓርቲ ወደ ስልጣን እንዲመጣ የተፎካካሪዎች ያለመጣመር ዋነኛ ምክንያት እንደነበር ተጠቅሷል።

ዋነኛ ተፎካካሪያቸው ቱንዱ ሊሱ እና ከማጉፉሊ ፓርቲ እራሳቸውን ያገለሉት የቀድሞ ሚኒስትር በርናርድ ሜምቤ እንሚሆኑ ግምት ተሰጥቷቸዋል።

አሁን በስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ ታንዛኒያ ነጻ ከወጣችበት ከ1961 ጀምሮ አገሪቱን በመምራት ላይ ይገኛል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.