ስፓርት

ቼልሲ ቲያጎ ሲልቫን አስፈረመ

By Tibebu Kebede

August 28, 2020

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚላዊው ተከላካይ ቲያጎ ሲልቫ የእንግሊዙን ቼልሲ ተቀላቀለ፡፡

ሲልቫ ለምዕራብ ለንደኑ ክለብ የማራዘም አማራጭ ያለው የአንድ አመት የኮንትራት ፊርማውን አኑሯል፡፡

የ35 አመቱ ተከላካይ ሰማያዊዎቹን በነጻ ዝውውር ከፈረንሳዩ ፒ ኤስ ጂ ተቀላቅሏል፡፡

ሲልቫ በዘንድሮው ክረምት የቼልሲ አራተኛው ፈራሚ ሆኗል፡፡

ከእርሱ ቀደም ብሎ ቲሞ ዌርነር፣ ሃኪም ዛይች እና ቤን ቺልዌል ስታምፎርድ ብሪጅ ደርሰዋል፡፡

ክለቡ የማላንግ ሳርን ዝውውርም ማጠናቀቁ ተነግሯል፡፡