Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እና የህንድ የቴክኖሎጂ ድርጅቶት በቅንጅት መስራት የሚያስችላቸውን ጥምረት መሰረቱ

ባለፉት አምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኢትዮ-ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ኤክስፖ ተጠናቋል።

በዚህም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ለመፍጠርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ በኢትዮጵያና ህንድ መካከል ተደርሶ የነበረው ስምምነት ወደ ትግበራ ገብቷል።

ባለፉት ስደስት ወራት ቅድሚያ በሚሰጣቸው ዘርፎች የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችና ድርጅቶች መረጣ እና ተመሳሳይነት ልየታም ሲካሄድ ቆይቷል።

በዚህ መሰረት 25 የህንድ የቴክኖሎጂ ባላሙያዎችና ድርጅቶች ከ57 የኢትዮጵያ ባለሙያዎችና ድርጅቶች ጋር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ጥምረት መመስረታቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኢትዮጵያ በቅንጅት በመስራት ታምናለች ያሉት ሚኒስትር ዴኤታ ጀማል በከር፥ የሁለቱ ሀገራት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ጥምርታ ውጤታማ እንዲሆን የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

የቴክኖሎጂው ዘርፍ የእውቀት ሽግግር እንዲያመጣ፣ ሃብት እና የስራ እድል እንዲፈጥር ለማድረግ ኢትዮጵያ ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢያዊ ሁኔታን እየፈጠረች እንደምትገኝም አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኑራንግ ስትራቫስታቫ በበኩላቸው፥ኢትዮጵያ እና ህንድ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የጀመሩት ስራ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክረው መሆኑን ተናግረዋ።

በኢትዮ-ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ፕሮግራም በሚቀጥሉት አምስት አመታት 50 ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን ለመፍጠር እቅድ መያዙ ተመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.