Fana: At a Speed of Life!

በህንድ በአንድ ቀን ከ78 ሺህ ሰዎች በላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህንድ በትናትናው ዕለት ብቻ 78 ሺህ 761 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተገለፀ።

ይህ በአሜሪካ በሐምሌ ወር በአንድ ቀን ከተመዘገበው ከፍተኛ ቁጥር በ1 ሺህ 462 ከፍ ይላል ተብሏል።

በህንድ ቁጥሩ በዚህ መጠን ከፍ ያለው ተጥለው የነበሩ እገዳዎች መነሳታቸውን ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል።

በጥቅሉ በህንድ እስከአሁን 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 63 ሺህ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

በተጨማሪም የሟቾቹ ቁጥር ከደቡብ አሜሪካ ሀገራት ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ መሆኑም ተነስቷል።

በትናትናው ዕለትም በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ25 ሚሊየን ሲበልጥ 843 ሺህ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.