Fana: At a Speed of Life!

ከአቶሚክ ቦምብ ከተረፉት የሂሮሽማ  ህንጻዎች  ሊፈርሱ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ1945 በጃፓን ሂሮሺማ ከተማ ከአቶሚክ ቦምብ  ፍንዳታ ከተረፉት ህንፃዎች ሊፈርሱ መሆኑ ተገለፀ።

በጃፓኗ ሂሮሺማ  ከተማ በአውሮፓውያኑ በ1945 በአቶሚክ ቦምብ ፍንዳታ ወቅት ከተረፉት ህንጻዎች መካከል  ሁለት ህንፃዎችን ለማፍረስ የታቀደ  መሆኑ ነው የተነገረው።

አንዳንድ  የአከባቢው ነዋሪዎች  ህንፃዎቹ መፍረስ እንደሌለባቸው እንዲሁም ለማስተማሪያነትና ለምልክት መቆየት አለባቸው ሲሉ ተሰምተዋል።

ከቦምብ ፍንዳተው በሕይወት የተረፉ አንድ ሰው፥ እነዚህን ህንጻዎች በመጠበቅ የኑክሌር መሣሪያዎች አስከፊነትና በወቅቱ የነበረውን መጥፎ ገጽታ ለትውልድ ማስተማር ያስፈልጋል ብለዋል።

ሁለቱ  ህንጻዎች ከተገነቡ በኋላ በመጀመሪያ በአውሮፓውያኑ 1913 ለወታደራዊ የልብስ ፋብሪካንት፤ በመቀጠልም ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መጠለያ በመሆን አገልግለዋል።

በተጨማሪም የቦምብ ፍንዳታ ከደረሰ በኋላ እንዱ ህንፃ  ሆስፒታል በመሆን ማገልገሉም ተገልጿል፡፡

በአቶሚክ  ቦምብ ፍንዳታው በሂሮሺማ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕንፃዎችን ማፍረሱ ይታወሳል።

በወቅቱ  የተረፉት  ህንጻዎች ከጠንካራ ኮንክሪት በመሰራታቸው መሆኑ የተገለፀ ቢሆንም፤ እስካሁን በህንጻዎች መስኮቶች እና በሮች ላይ የቦምብ ጥቃቶች  ምልክቶቹ እንዳሉ ይታያሉ ተብሏል፡፡

በቦምብ ፋንዳታውም  80 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች  ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን 35 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል፡፡

በፈረንጆቹ  2017 የሀገሪቱ ባለስልጣናት  ህንጻዎቹ በጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ የመጠቃት ዕድላቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ነበር።

ሕንፃዎቹ አገልግሎት ላይ ያልዋሉ እና ለህዝብ ክፍት ባለመሆናቸው የአከባቢው መንግስት በ2022 እንዲፈርስ መወሰኑ ተነግሯል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.