Fana: At a Speed of Life!

የግብርናውን ዘርፍ ለመቀየር የግሉ ዘርፍ የፈጠራ ሚና ጉልህና አስፈላጊ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያን በግብርና ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት የግሉ ዘርፍ የፈጠራ ሚና ጉልህና አስፈላጊ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

በኢኮኖሚው ውስጥ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት እየተሠራበት ያለው አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ግብርናው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

በኢትዮጵያ የዘመናዊ ግብርና ትምህርትና ምርምር ከተጀመረ ከ70 ዓመታት በላይ እንደሆነው የገለፁት ጠቅላይሚኒስሩ፥ ሆኖም እስካሁን ግብርናው ከበሬ ስበት፣ ከገበሬ ጉልበት በመላቀቅ ወደ ኢንዱስትሪ ግብዓትና የወረት ክምችት ሽግግር አላደረገም ብለዋል።

ይህንን ለመቀየር ደግሞ የግሉ ዘርፍ የፈጠራ ሚና ጉልህና አስፈላጊ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.