የሀገር ውስጥ ዜና

የግብርናውን ዘርፍ ለመቀየር የግሉ ዘርፍ የፈጠራ ሚና ጉልህና አስፈላጊ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ

By Tibebu Kebede

August 31, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያን በግብርና ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት የግሉ ዘርፍ የፈጠራ ሚና ጉልህና አስፈላጊ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

በኢኮኖሚው ውስጥ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት እየተሠራበት ያለው አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ግብርናው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።