Fana: At a Speed of Life!

ሀገራት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚወስዷቸውን የደህንነት እርምጃዎች መቀጠል አለባቸው- የአለም ጤና ድርጅት

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 26፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የሚወስዷቸውን የደህንነት እርምጃዎችን እንዲቀጥሉ የዓለም ጤና ድርጅት አሳስቧል፡፡

የንግድ እንቅስቃሴዎችን እና ሌሎች አገልግሎቶችን በድጋሜ ለመክፈት ዝግጅ እያረጉ የሚገኙ ሀገራት ህዝባዊ ስብሰባዎችን መገደብ እና ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎችን መጠበቅ እንዳለባቸው ድርጅቱ አስታውቋል ፡፡

ሀገራት ንግዶችን እና የተለያዩ እንቅስቃሴወችን ክፍት ማድረግ ካለባቸው ስርጭቱ እንዳይስፋፋ እንዲሁም ህይወትን ለማዳን መወሰድ ያለባቸውን ጥንቃቄዎች በመተግበር መሆን እንዳለበት ተጠቁሟል።

የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠር የቻሉ ሀገራት እንቅስቃሴዎን መጀመር ይችላሉ ያለው ድርጅቱ በተቃራኒው ቁጥጥር ሳያደርጉ የተለያዩ አገልግሎቶችን እና መሰባሰቦችን ማስጀመር የከፋ ቀውስ እንደሚፈጥር የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገልፀዋል፡፡

አሁንም ቢሆን በስታዲየም፣ በምሽት ክለቦች እና በእምነት ቦታዎች ባለመሰባሰብ እንዲሁም ሌሎች መፍትሄዎችን በመውሰድ ሀገራት ወረርሽኙን መቆጣጠር እንደሚገባቸው ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

በተለይም ሀገራት ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በቫይረሱ ምክንያት ከመሞት መታደግ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

እያንዳንዱ ሰውም የፊት እና የአፍ ጭንብልን በአግባቡ በማድረግ፣ ርቀትን በመጠበቅ እና እጅን በተደጋጋሚ በመታጠብ የበኩላቸን ድርሻ መወጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፡- ሲጂቲኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.