ቢዝነስ

የመስከረም ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

By Meseret Demissu

September 01, 2020

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመስከረም ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር ባለበት እንደሚቀጥል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደርግ እንደሚችል  ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በመስከረም ወር በሊትር በ26 ብር ከ97 ሳንቲም እንዲሸጥ መወሰኑን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።