ኢትዮጵያ በስርዓተ-ጾታ መካከል ያሉ ልዩነቶችን በመቀነስ ከፍተኛ ለውጥ ማስመዝገቧን ጥናት አመለከተ
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 9፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ በስርዓተ-ጾታ መካከል ያሉ ልዩነቶችን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ለውጥ ማስመዝገቧን ጥናት አመላክቷል።
በወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም የ2020 የዓለም አቀፍ ጥናት መሰረት በስርዓተ-ጾታ መካከል ያሉ ልዩነቶችን በመቀነስ በዓለም ከፍተኛ ለውጥ ካስመዘገቡ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗ ተገልጿል።
በዚህም ኢትዮጵያ ከዓለማችን 153 ሀገራት ውስጥ 70 ነጥብ 5 በመቶ በማስመዝገብ በስርዓተ ጾታ መካከል ያሉ ልዩነቶች በመቀነስ በዓለም 82ኛ ደረጃን መያዝ ችላለች።
በዚህ ዓመት በዓለም አቀፍ ደረጃ በስርዓተ-ጾታ መካከል ያሉ ልዩነቶች በመቀነስ ኢትዮጵያ ፣ ስፔን ፣ ማሊ፣ አልባኒያ እና ሜክሲኮ ከፍተኛ ለውጥ ማስመዝገባቸውን ከሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።