Fana: At a Speed of Life!

ሳዑዲ ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና እስራኤል የአየር ክልሏን ፈቀደች

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሳዑዲ አረቢያ በዛሬው ዕለት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና እስራኤል በአየር ክልሏ በኩል ለሚያደርጉት በረራ ፍቃድ መስጠቷን አስታወቀች፡፡
ሳዑዲ ከዚህ ቀደም መነሻና መድረሻቸውን እስራኤል የሚያደርጉ በረራዎች ላይ በአየር ክልሏ በኩል እንዳያልፉ እገዳ ጥላ ቆይታለች፡፡
 
ሀገሪቱ የአየር ክልሏን የፈቀደችው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከእስራኤል ጋር መደበኛ ዲፕሎማሲ መመስረቷን ተከትሎ ባነሳችው ጥያቄ መሰረት ነው ተብሏል፡፡
 
ውሳኔው በሁለቱ አገራት መካከል የሚደረገውን የአየር በረራ ጊዜ ያሳጥራል ተብሏል፡፡
የሳዑዲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሳል ቢን ፋራኻን አል ሳዑድ በፍልስጤም ላይ ያላቸው አቋም እንዳልተለወጠ ገልጸዋል፡፡
 
ከሁለት ቀናት በፊት የአሜሪካንና የእስራዔል ልዑካንን የያዘ አውሮፕላን በሳዑዲ የአየር ክልል በኩል ከቴል-አቪቭ ተነስቶ አቡዳቢ መድረሱ ይታወሳል፡፡
 
ምንጭ፦ ሬውተርስ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.