የሀገር ውስጥ ዜና

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ህገ ወጥ የግንባታ ፍቃድ ለመስጠት 140 ሺህ ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሃላፊ በቁጥጥር ስር ዋሉ

By Meseret Demissu

September 03, 2020

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 28 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲበንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 03 አስተዳደር የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ጽኅፈት ቤት ህገ ወጥ የግንባታ ፍቃድ ለመስጠት140 ሺህ ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ።

ባለጉዳዩ ለከንቲባ ጽህፈት ቤት እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባደረሱት ጥቆማ ÷ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር በተደረገ ክትትል የጽህፈት ቤት ሃላፊውን ገንዘቡን ሲቀበል በቁጥጥር ስር መዋሉን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወንጀል ክትትል ሃላፊ ኮማደር አወሉ አህመድ ተናግረዋል።