Fana: At a Speed of Life!

ጳጉሜን አንድ የሳይክልና የእግረኞች ቀን ሆኖ ይውላል- የትራንስፖርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጳጉሜን አንድ የሳይክል እና የእግረኞች ቀን ሆኖ እንደሚውል የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ቀኑ በአገር ደረጃ በሁሉም ክልል ዋና ከተሞችና በሌሎች አካባቢዎች የሚከበር መሆኑንም ነው ሚኒስቴሩ የገለፀው።

ይህም አመቱን ሙሉ ወር በገባ በመጨረሻው እሁድ የሚከናወን መሆኑንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በእግር እና ብስክሌት የሚደረግ ጉዞ የሞተር አልባ ትራንስፖርት በመሆናቸዉ የትራፊክ መጨናነቅና አደጋዎችን ለመቀነስ፣ የአካባቢ አየር ብክለት ችግሮችን ለማቀነስ፣ የማህበረሰቡ ጤናም እንዲጠበቅና ተመራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት ፍላጎት ጥያቄዎችን በማስተናገድ የበኩሉን የሚያበረክት የትራንሰፖርት ዘርፍ መሆኑንም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።

በሌላ በኩል የትራንፖርት ሚኒስቴር የሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂን ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅቱን መጠናቀቁን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.