አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመጪ ወራት ለወባ በሽታ መከሰት ምቹ የአየር ሁኔታ በመኖሩ በሽታው በሚከሰትባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የጤና ሚንስቴር አሳሰበ።
የሚንስቴሩ የብሄራዊ የወባ ፕሮግራም አስተባባሪ መብራህቶም ሃይለ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የብሄራዊ ሜትሮሎጂ ትንበያን መሰረት በማድረግ ዝናባማ የአየር ጠባዩ እስከ መስከረም አጋማሽ ሊቆይ ስለሚችልና ይህም ለወባ ትንኝ መፈልፈያ የሚሆኑ የተቋጠሩ ውሃዎችን ሊፈጥር ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲደረግ አስገንዝበዋል።