የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 24 ሰዓታት 1ሺህ303 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ24 ሰዎች ሕይወት አልፏል

By Feven Bishaw

September 04, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 23 ሺህ 712 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 303 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 56 ሺህ 516 መድረሱንም የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያወጡት መረጃ ያመለክታል።