የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ በ362 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ 197 ፕሮጀክቶች ወደ ስራ ገቡ

By Tibebu Kebede

September 05, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በ362 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ 197 ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

የልማት ፕሮጀክቶቹ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ እና በክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ካሳሁን እና በሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል፡፡