Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ያመጠቀቻት ሳተላይት ምድርን መቃኘት ጀመረች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ያመጠቀቻት ሳተላይት ምድርን መቃኘት መጀመሯን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ምድርን እየቃኘች እና በፎቶ እየመዘገበች መረጃ የምትሰበስበው “ETRSS-1” በዛሬው ዕለት ነበር ወደ ህዋ የመጠቀችው።

ሳተላይቷ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር፣ ከግብርና ጋር የተያያዙ ጥናት እና ምርምሮችን ለመስራት እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ለማከናወን የሚያስችሉ መረጃዎችን ትልካለች ነው የተባለው።

ሳተላይቷ በቻይና ከሚገኝ የማምጠቂያ ማዕከል ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች በተገኙበት ወደ ህዋ የመጠቀች ሲሆን፥ በአዲስ አበባ ውስጥም ይህን ታላቅ ታሪካዊ ክስተት የሚዘክሩ በርካታ ዝግጅቶች እየተከናወኑ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሳተላይቷ በዋናነት ግብርናውን ለማዘመን በእውቀትና በመረጃ ላይ በመንተራስ ስራዎችን ለመስራት የምታግዝ፣ በአፍሪካና በዓለም ገበያ በእውቀት ላይ በመመስረት ለመወዳደር እና ውጤታማ ለማድረግ ታስችላለች ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.